ጳውሎስ ሲጽፍ "....ወይስ....የቸርነትን... ባለጠግነት....ትንቃለህን? " ሲል ይጠይቃል፡፡ "መናቅ" የተባለው ቃል አቅልሎ አሳንሶ ማየት ማለት ነው፡፡ ግሱ ዝቅ አድርጎ ማጣጣልን፣ ማራከስን ማዋረድን፣ መሳለቅን፣ አሽቀንጥሮ መጣልን ያመለክታል፡፡ ለመሆኑ የእግዚአብሔር ቸርነት እውነተኛ ዋጋ ታውቃለችሁ? ቸርነቱ ዋጋው ምን ያህል ነው?
የዚህ ዘመን ትውልድ ጥቂት ችግር ሲያጋጥመው እምነቱን አሽቀንጥሮ ጥሎ እግዚአብሔርን "ጨካኝ ምላክ" ብሎ እስከማሰብ የሚደርስ ህብረተሰብ ነው፡፡ ሰዎች በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚከሰቱትን ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ የሆኑ ጥፋቶችን እየተመለከቱ፣ ለምሳሌ፣ በርዕደ ምድር አደጋ ሩብ ሚልዮን ሕዝብ በአንድ ጊዜ የምቱበትን የሃይቲን አደጋ አይተው፣ ፓኪስታንን፣ ወይም የዝናብና የጎርፍ መጥለቅቅ የተከሰተባቸውንና በመቶ ሺ ዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎቻቸው በምትና በበሽታ በመፈናቀል የሞቱባቸውን ሕዝቦች አይተው፣ ወይም በሱናሚ አደጋ ሚሊዮኖችን ያጡ እንደ ኢንዶዥያ ያለ ሃገራትን አይተው፣ "እግዚአብሔ እንዴት እንዲህ ያለ ነገር እንዲሆ ይፈቅዳል?" "እግዚአብሔር ምን አይነት አምላክ ነው?" ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ የእግዚአብሔርን ፍርድ ያያሉ፣ ከዚህም የተነሳ እግዚአብሔር በጣም ጨካኝና ያለ ምህረት፣ ያለ ቸርነት ያለ አምላክ መሆን አለበት ሲሉ ይደመድማሉ፡፡
ከእውነቱ የሚያመልጥና የሚወጣ ግን ምንም የለም፡፡ እውነቱም በነዚህና መሰል ጥፋቶች እንዲጠፋ የተደረጉ ኃጢአቶኞች መጥፋት የነበረባቸው ከረጅም ጊዜ በፊት መሆኑ ነው፣ ይህ ትክክል አይደለምን? "የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነው"፡፡ እውነታው እስከዚያች ቀንና ሁኔታ ድረስ የኖሩት የምህረቱ ጊዜ ስለተረዘመ ብቻ ነው፡፡ እኛም ብንሆን በሕይወት የምንኖረው ከነርሱ በሚያጠፋው መአት ከጠፉቱ የተሻልን ሆነን ተገኝተን ሳይሆን የንስሃን እድል እንድናገኝ የምህረቱን ጊዜ ስላራዘመልን ብቻ ነው፡፡ በሰሊሆም ግንቡ የወደቀባቸውን፣ ጲላጦስ ደማቸውን ከመስዋእታቸው ጋር የደባለቀውን ሰዎች ጉዳይ አንስቶ እነዚህ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሰዎች ሁሉ የሚብሱ እንዳልሆኑ በሰጠው ማስጠንቀቂያ "ንስሃ ባትገቡ ሁላችሁ እንዲሁ ትጠፋላችሁ" የሚለው ዋና መልእክቱ ነው።
እዚህ ጥቅስ ላይ ይህንን መለኮታዊ ቸርነት አቅልለን እንዳናየው፣ እንዳንንቀው፣ የእግዚአብሔን ባለጠግነት እንዳናሳንሰው፣ የባለጠግነቱን፣ የመቻሉንና የትዕግስቱን ዋጋ ዝቅ አድርገን እንዳንመለከት ተነግሮናል፡፡ ደግነቱን፣ መልካምነቱን፣ ተቀባይነቱን መለኮታዊ ቸርነቱን አንናቅ። መቻል (Tolerance) የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሳይፈርድ ታግሶ ሰላምን በማድረግ መቆየትን ነው። ይኸውም መጨከን ሲገባው አልጨከነብንም ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት እግዚአብሔር ቁጣውን መልሶ ሳይፈርድ ሳያጠፋን አልፎናል፣ በረከቱንም ሰጥቶናል ማለት ነው። እግዚአብሔር ማለቂያ በሌለው ትዕግስቱ ለብዙ ዘመን በጎነታችንን የሚሻና ለእኛም በጎ ነገርን በማድረግ የሚደሰት ሆኖ ኖሮአል (log-sutferirg) የእግዚአብሔር ፍትህና ጽድቅ ስለ ኃጢአታችን ወዲያው እንዳይቀጣንና እንዳይፈርድብን ቸርነቱ እንዲሸከመን፣ እንዲችለንና እንዲታገሰን ግድ ይለዋል። ተበቃይነቱንና ጭከናውን ለብዙ ዘመን ገቶና ከልክሎ ይዞታል።
እግዚአብሔር በባህርዩ መልካም ኃጢአተኞችን የሚታገስና የሚጠቅም አምላክ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የወል ጸጋ (common graca ) የሚባለው ነው "እርሱም በክፉዎችና በጻድቃን ላይ ጸሐይን ያወጣል ዝናብንም ያዘንባል" እርሱ ይታገሳል ማለት ኃጢአተኞች የሚገባቸውን የጽድቅ ቅጣት ፍትሃዊ ፍርድ ጠብቆ ያቆያል፣ ይህንንም ለረጅም ዘመን ያደረጋል ማለት ነው፡፡ ይህንን የወል ጸጋ ከእምነት የራቁ ከሃዲዎችም እንኳ በምድር ላይ ዘመናቸው ሲጠቀሙ ይኖራሉ፤ ታዲያ የብልጽግና ወንጌል ሰባክያን ("ካድሬዎች" ብላቸው ደስ ይለኛል) በብርና በወርቅ መንበሽበሽን ለምን እንደትልቅ ነገር ያዩታል? ገንዘብን የሚያመልኩ ምድራዊ ሃሳብ ብቻ ስላላቸው አይደለምን?
ኃጢአተኞች ይኖራሉ፣ ኃጢአተኞች ይበለጥጋሉ፣ ኃጢአተኞች በኑሮ ደስ ይላቸዋል፣ በሕይወት ተባርከዋል፣ በጊዜያዊ በረከት፣ በምድራዊ በረከት፣ ብሕይወትና በኑሮ ደስታ ተንበሽብሸዋል። የብልጽግናን ወንጌል ሰብከን ማናቸውንም ወደ ዘላለም ሕይወት ልንመራ የማንችለው ስብከታችን የሌላቸውን ስለማይነግራቸው ነው።
እግዚአብሔር ግን ፈጽሞ ሊያጠፋን የሚያስችለው ማንኛውም አሳማኝና ትክክለኛ ምክንያት ነበረው ደግሞም አለው፣ መላውን የሰው ዘር ባንድ ጊዜ እልም አድርጉ ለመጨረስ የሚያስችለው ማንኛውም ምክንያት እግዚአብሔር አለው፡፡ ነገር ግን ቸርነቱና መቻሉ አዎንታዊ የሆኑ በረከቶችን በኃጢአተኞች ኑሮ ላይ እንዲያትረፈርፍ ፍርዱንም አቆይቶ እንዲያዝ አርድጎታል፡፡
አይሁድ የእግዚአብሔን ቸርነት እንደ መብት ወስደውታል፡፡ ዛሬም ቢሆን ሰዎች እንደ መብት ያዩታል፡፡ ፍቅርንና ወዳጅነትን፣ ውበትንና ድሎትን፣ ምቾትንም፣ ምግብንና መጠጥን፣ ልብስንና ተፈጥሮን፣ ልጆችንና ተድላን እንደ መብት ያዩታል። የሚኖሩት ግን በምህረት ነው፡፡ የሚኖሩት በእግዚአብሔር ደግነት ነው፡፡ እርሱ ባርኮአቸውና ፍርዱንም አቆይቶላቸው ይኖራሉ። በእንደዚያ አይነት ኑሮ ለብዙ ዘመን እጅግ ተመችቶአቸው ጸጋውን ተቀብለው ሳለ ራሳቸውን እንደተገባቸው ባለመብቶች እየቆጠሩ ኖረዋል፡፡
በምድር ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ስላለ እግዚአብሔርን ጨካኝ ነው ብለው ለሚያስቡ ሰዎች፣ ሱናሚ ስላለ እግዚአብሔን አይራራም ለሚሉ ሰዎች፣ አንድ ሰው በካንስር ስለተያዘ እግዚአብሔር አይራራም ለሚሉ ሰዎች፣ ሰዎች በሽብር አደጋ ስለሚሞቱ እግዚአብሔር ጨካኝ ነው ለሚሉ ሰዎች፣ ይህ ነጥብ እግዚአብሔር መሃሪ፣ ፍርዱንም የሚጠብቅ፣ ምህረቱንም በማይገባቸው ላይ የሚያፈስ መልካም አምላክ ነው እንዲሉና እንደመለሱ የሚያደርግ ነጥብ ነው፡፡
ዊልያም ጉርናል በ1600 አ.ም ሲጽፍ "የሚበዛው የሰው ዘር የእግዚአብሔርን ቸርነት አቃሎ እንደተናቀ አድርጎ ሲቆጥረው ሳይ በአለም ሁሉ ወደር የማይገኝለትና ከተአምራት ሁሉ የሚበልጠው ተአምር በዚህ ክፋ አለም ላይ የበዛው የእግዚአብሔር ትዕግስትና ቻይነቱ ነው ከማለት በቀር ምንም ማለት አይቻለኝም" ብሎአል። ቆም በሉና እግዚአብሔር ያሳያችሁን የበጎነቱን ብዛት አስቡ፡፡ ይህንን በተመለከተ ምን ያደረጋችሁት ነገር አለ? እየማጋችሁ ያላችሁት የእርሱን አየር፣ እየሞቃችሁ ያላችሁት የእረሱን ጸሐይ፣ እየበላችሁ ያላችሁት የእርሱን ምግብ፣ እየለበሳችሁ ያላችሁት የእርሱን ልብስ፣ እየኖራችሁ ያላችሁት በእርሱ ቤት፣ ተዘልላችሁ የተቀመጣችሁት በገዛ ራሱ ምድር፣ የምታርሱት የምትዘሩት በእርሱ መሬት፣ የምታጭዱት የምትሰበስቡት ከእርሱ እርሻ፣ እይሰራችሁ ያላችሁት በእርሱ መስርያ ቤት፣ ወይም እየተማራችሁ ያላችሁት በእርሱ ትምህርት ቤት ነው እኮ! እስቲ አስቡ የእርሱ የብቻው ያልሆነ ምን አለ?
"ምድርና ሞላዋ ለእግዚአብሔር ናት፥ ዓለምም በእርስዋም የሚኖሩ ሁሉ።" መዝሙር 24፥ 1
እግዚአብሔር መልካም ነው፣ይህ መልካምነቱ ወደ ንስሃ ሊመራ ይገባናል፡፡ በግንባርህ ውደቅና እየሰገድህ"እንደበደላች አልተከፈለንም" በልና ዘምር!!
No comments:
Post a Comment