የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ
አጭር ዳሰሳ
አጭር ዳሰሳ
በመጽሐፉ ትርጉም ላይ መደረግ ስላለበት የአስተሳሰብ ለውጥ
ጠቋሚ የሆኑ አንዳንድ ነጥቦች
ጠቋሚ የሆኑ አንዳንድ ነጥቦች
የራእይን መጽሐፍ ስናጠና ከዘመን አኳያ መመለስ ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ፦
መጽሐፉ የሚያወራው ያለ በቂ ጥናት በተለምዶ ሲታሰብና ሲታመን እንደነበረው፣ እኛ ካለንበት ከዚህ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን አንጻር ሲታይ ስለ መጻኢው ማለትም ስለ ወደፊቱ ነው? ወይንስ በተቃራኒው ስለ ኃላፊው? ማለትም በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ተፈጽሞ ስለ አለፈ ጉዳይ፣ ስለ የትኛው ዘመን ነው?
የዚህን መሰረታዊ ጥያቄ መልስ ለመወሰን መመለስ ያለባቸውን ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ጥያቄዎች ከራሱ ከመጽሐፉ እያነሳን በራሱ በመጽሐፉ መመለስ ይኖርብናል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሳይጣረስና ሳይጣላ መፈታትና መተርጎም ያለበት በራሱ "በእግዚአብሔር ቃል ብቻ" ነው እንጂ፣ በርካቶች በስብከታቸውና በትምህርታቸው ብሎም በመዝሙራቸው እንደሚያንጸባርቁት በዚህ በአሁኑ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አለም፣ በየእለቱ በመገናኛ ብዙሃን በምንሰማውና በጋዜጦች በምናነበው ትኩስ ዜና፣ በመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ውዝግብም ሆነ በየትኛውም ልዕለ ኃያል ሃገርና መንግስት የፖለቲካ ትኩሳት መተርጎም አግባብ አይደለም።
ሌላ ተያያዥ ጥያቄ፣ የራዕይ መጽሐፍ የሚናገረው መጽሐፉ ከተጻፈበት የመጀመርያው ክፍለ ዘመን አንጻር ከረጅም ዘመን በኋላ ምናልባትም ገና ከዚህ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ስለሚሆኑ ሁነቶች ነው ከተባለ፣ ታዲያ በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የንባብ ክፍሎች የሚያነሱአቸው ጉዳዮች ለምን በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ከነበረችው እስራኤል ጋር የሚገናኙ ሁነቶች ሆኑ?
እነዚህም በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ከነበረችው እስራኤል ጋር የሚገናኙ ሁነቶችን የሚያመለክቱ ከዚህ በታች የተጠቀሱ የንባብ ክፍሎች የተሰጡባቸውን አውድ ለቃሉ ብቻ ታማኝ ሆነን በጥንቃቄ ብንመለከት፣ ትንቢቱ ሲነገርና መጽሐፉ ሲጻፍ የሚፈጸምበትንም የጊዜ ማእቀፍ እያመለከተ የተሰጠ ቃል መሆኑን ጨምረን እናስተውላለን።
በመጽሐፉም ውስጥ በተለይ ልናስተውላቸው የሚገቡንን አራት ነጥቦች ላንሳላችሁ ( እነዚህም ለዚህ አጭር የመግቢያ ጥናት ብቻ በወፍ በረር ላነሳቸው የምፈልጋቸው ነጥቦች ናቸው)፦
(ሀ) በመጽሐፉ ውስጥ በግልጽ የተቀመጡ ጊዜን አመልካች የሆኑ ምንባባት ያሉ መሆናቸውን ልብ በሉና ተመልከቱ፣
(ለ) በግልጽ ተወስኖ ከተሰጠና ጊዜን አመልካች ከሆኑ ከሌሎች የአዲስ ኪዳን ምንባባት ጋር ዝምድና ያላቸው ምንባባት የሚገኙበት መሆኑንም አስተውሉ
(ሐ) በተለይ ጥንታዊዋንና የቀድሞውን ኪዳን ኢየሩሳሌምን ወይም የእስራኤልን ሕዝብ በማመልከት አንጻር የተነገሩ ምንባባት ያሉበት መሆናቸውንም ተመልከቱ፤ እንዲሁም
(መ) የመጀመሪያይቱ ክፍለ ዘመን ኢየሩሳሌም በወቅቱ ከነበረችበት አይነተኛ የአይሁድ ማህበረሰብ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ጋር በራእዩ መጽሐፍ የተገለጡ አይነተኛ ቦታዎችና ዘመኑ የተገናዘቡ መሆናቸውንም ተረዱ።
የሚከተሉትን የንባብ ክፍሎች ከፍ ሲል ከተጠቀሱት 4 ነጥቦች አንጻር መጽሐፍ ቅዱሳችሁን እያመሳከራችሁ በጥንቃቄ ትመለከቱአቸው ዘንድ እጋብዛለሁ፦
ራእይ ምዕራፍ 1 ቁ. 1 "ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥ "
ቁ.3 "ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው። "
ቁ.7 "እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። "
ቁ.9 "እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ"
ቁ.10 "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥"
ቁ.19 "እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ"

ራእይ ምዕራፍ 2 ቁ. 10 "ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ። "
ቁ.16 "እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።"
ቁ.25 "ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።"
ቁ.16 "እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።"
ቁ.25 "ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።"
ራእይ ምዕራፍ 3 ቁ. 10 "የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።"
ቁ .11 "እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።"
ቁ .11 "እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።"
ራእይ ምዕራፍ 4 ቁ. 1 "ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።"
ራእይ ምዕራፍ 6 ቁ.16-17 "ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው። "
ራእይ ምዕራፍ 8 ቁ.13 "አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ፦ ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።"
ራእይ ምዕራፍ 8 ቁ.13 "አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ፦ ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።"
ራእይ ምዕራፍ 10 ቁ.6-7 "ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ። ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ። "
ራእይ ምዕራፍ 11 ቁ. 1-2 "በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ፦ ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ። በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።"
ቁ. 8 "በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።"
ቁ.15-19 "ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ፦ ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤ አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ። በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።"

ራእይ ምዕራፍ 12 ቁ. 5 "አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።"
ራእይ ምዕራፍ 14 ቁ.7 "በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ። "
ቁ.14-20 "አየሁም፥ እነሆም ነጭ ደመና፥ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፥ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው። ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፦ የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፥ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው ምድርም ታጨደች። ሌላ መልአክም በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፥ እርሱም ደግሞ ስለታም ማጭድ ነበረው። በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ። መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፥ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር ቍጣ መጥመቂያ ጣለ። የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፥ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ። "

ራእይ ምዕራፍ 15 ቁ 5-8 "ከዚህም በኋላ አየሁ፥ የምስክርም ድንኳን መቅደስ በሰማይ ተከፈተ፥ ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ጥሩ የጌጥ ልብስ ለበሱ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ። ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአብሔር ቍጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው። ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኃይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፥ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም።"
ራእይ ምዕራፍ 16 ቁ.6 "የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፥ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።"
ቁ. 19 "ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።"
ቁ. 19 "ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።"
ራእይ ምዕራፍ 17 ቁ.8 "ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ። "
ራእይ ምዕራፍ 18 ቁ.24 "በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።"
ራእይ ምዕራፍ 20 ቁ. 7-10፣ "ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፥ በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው። ወደ ምድርም ስፋት ወጡ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው። ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ። "
ቁ. 11-15 "ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም። ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ። ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ። ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው። በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ። "

ራእይ ምዕራፍ 22 ቁ.6-7 "እርሱም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፥ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ። እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ። "
ቁ. 10 "ለእኔም፦ ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።"
ቁ.12፣ "እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።" ቁ. 20 "ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።"
ቁ. 10 "ለእኔም፦ ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።"
ቁ.12፣ "እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።" ቁ. 20 "ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።"
ከነዚህ ምንባባት መካከል አንዳንዶቹ ጊዜን በማመልከት አንጻር በግልጽ የተቀመጡና ሊሆኑ ያሉትን ሁነቶች የሚያመለክቱ ሲሆኑ እነርሱም "ቶሎ" ወይም ቅርብ ወይም ሳይዘገዩ የሚፈጸሙ ጉዳዮች መሆናቸውን ያሳያሉ። በተጨማሪም ከነዚህ ምንባባት መካከል አንዳንዶቹ በግሪኩ 'mello' የተሰኘውን ቃል ይዘዋል (1፥ 19፤ 3፥ 10፤ 8፥ 13፤ 10፥ 7፤ 22፥ 10፣ 12፣ 20 ተመልከቱ) ይኸውም "ይሆን ዘንድ ያለው" ("abaut to be") ተብሎ ተተርጉሞአል። ቃሉም አንዳች የሚጠባበቁት ጉዳይ ሳይዘገይና ምንም ጊዜ ሳይወስድ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊፈጸም ቀነ ቀጠሮ የተቆረጠለት መሆኑን ያመለክታል።
ይህ ጊዜን አመልካች የሆነው ንግግር በመላው የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ፣ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ፣ በመሐል እና በመጽሐፉ ማጠቃለያ ላይ ተደጋግሞ መጠቀሱ ትንቢቱ አንድ ወጥ ሆኖ ሳይነጣጠልና ሳይከፋፈል በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ ይኸውም "ቶሎ"፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈጻሚ የሚሆንበትን አይነተኛ ጊዜ የሚያመለክት ነው። ይህም "ቶሎ" የትንቢቱ ተቀባዮች በኩረ ተደራስያኑ ገና በህይወት ሳሉ በትዉልዳቸዉ ውስጥ የሚደርስ ቶሎ ነው እንጂ የዚህ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የእኛ ቶሎ አይደለም። ይኸውም ደግሞ ጌታችን በስጋው ወራት እየደጋገመ ለተከታዮቹ ያስተማራቸውን ፍካሬውን የሚያስተጋባ ንግግር ነው። "እውነት እላችኋለሁ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል"፣ "ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም"፣ "የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ"፣ "እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም"፣ "የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ" ...ወዘተ።
ስለዚህ ማንም ቢሆን በዚህ የትንቢት መጽሐፍ ላይ አውድ ዘለል የሆነ ትርጉምን ተከትሎ ስህተትን ሳይፈጽም የነዚህን ሁነቶች ፍጻሜ ሊከፋፍልም ሆነ የትንቢቱን ፍጻሜ ከተጻፈበት የመጀመርያው ክፍለ ዘመን አንጻር በብዙ የዘመን ርቀት አራዝሞ አሁንም ሆነ ወደፊት ሊጠባበቅ አይችልም።
በቀጣዩ ጽሑፌ የራእይ መጽሐፍ ስለተጻፈበት ጊዜ አነሳና ጊዜውን አስመልክቶ ያለው ሙግት በምንከተለው አመለካከት ላይ የሚያሳርፈውን ተጽእኖ ለመዳሰስ እወዳለሁ። ለአሁን በጽሑፍ ርዝመት እንዳንሰለቻች በዚሁ ይብቃን። ቸር ሰንብቱ!
#########
#########
ያለፉና አሁን ያሉ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት መጽሐፉ ከ70 ዓ.ም በፊት መጻፉንና እንዲሁም የኢየሩሳሌምንና የቤተ መቅደሱን ውድመት ከበው ያሉ ሁነቶችን በተመለከተ የተነገረ መሆኑን ያምናሉ።
የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ገና አሁንም ወደፊት በብዙዎች ሰለሚጠበቀውና መጻኢ ስለሆነው ስለ "መጨረሻው ቀን" የተነገረ ከሆነ፣ ታድያ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በብዙ ስፍራ ስለ መጨርሻው ቀኖች የተነገሩ ክፍሎች ለምን በግልጽ የመጀመሪያውን ክፍለ ዘመን ያመለክታሉ? ለምሳሌ ቀጥሎ የቀረቡትን ጥቅሶች አመሳክሩ፦
ሐዋ 2፥ 14-20፤ ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፥ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦ አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤ ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው። እግዚአብሔር ይላል፦ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤ ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤ ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።

1ጢሞ 4፥ 1፤ መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤....
2ጢሞ 3፥ 1፤ ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
እብ 1፥ 2፤ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤
እብ 1፥ 2፤ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤
ያዕ 5፥ 3-9፤ በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል። እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም። እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም ነገር ግን፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤ እንደዚህም በሌላ ስፍራ ደግሞ፦ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል። እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።
1ጴጥ 1፥ 5፣ 20፣ ፤ ...ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።.....ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፥ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።
2ጴጥ 3፥ 3፤ በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤
1ዮሐ 2፥ 18፤ ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን
ይሁዳ 18 እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ የያዛቸው ሁነቶች መጽሐፉ ከተጻፈበት ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን በዘለለ ከሺህዎች አመታት በኋላ የሚሆኑና የሚፈጸሙ ጉዳዮች ከሆኑ፣ የዮሐንስ በራእዩ ስለ "ስድስተኛው ንጉስ" በተናገረ ጊዜ ለምን "አንዱም አለ" ሲል ይናገራል?
ራእ 17፥ 10 "ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።"
ራዕዩ በተለይ ስለ ሰባት ነገስታት ጠቅሶ ይናገራል፡፡ "አምስቱ ወድቀዋል" የተባሉት፣ ይኸውም ራዕዩ ከመሰጠቱና ከመጻፉ በፊት ተፈራርቀው የነገሱት ነገስታት ናቸው፡፡ "አንዱም አለ"፣ ይህ በአሁን ጊዜ አመልካች ንግግር የተጠቀሰውና "አለ" የተባለው ራዕዩ ሲጻፍና ሲሰጥ ይገዛ የነበረው ንጉስ ነው፡፡ ሰባተኛው ገና አልመጣም ሲመጣም ብዙ አይቆይም የተባለው ነው፣ እርሱም ከራዕዩ መሰጠትና መጻፍ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡
ዮሐንስ በራእዩ ምዕራፍ 14፥ 7 ላይ "የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና" ብሎ ሲናገር፣ እርሱ ከነበረበት ጊዜ በብዙ ርቀት ገና ወደፊት ስለሚመጣ ጊዜ ሊያመለክት እንዴት ይቻለዋል?
144,000ዎቹ (ራእ 7፥ 14) ከሺህዎች አመታት በኋላ ስለሚታተሙ ሰዎች የተነገረ ከሆነ, ታድያ የንባብ ክፍሉ በኩራት ናቸው ሲል ለምን ይናገራል?
መከራውስ ቢሆን ዮሐንስ ከነበረበት ጊዜ አንጻር ገና ወደፊት ያለና የሚጠበቅ ነገር ከሆነ፣ ታድያ ራእዩን እየጻፈ በነበረበት ጊዜ ያኔውኑ እርሱ ራሱም ቢሆን በመከራው ውስጥ እንደነበር ለምን ይናገራል (ራእ 1፥ 9)?
የራእዩ መጽሐፍ ሁነቶች የሚፈጸሙት ከተጻፉበት ጊዜ አንጻር ገና ወደ ፊት ብዙ ዘመን ቆይተው ከሆነ ታዲያ ዘመኑ ቀርቦአልና የመጽሐፉን ቃል በማህተም አትዝጋው የሚልን መመርያ ለምን ተቀበለ (ራእ 22፥ 10)?
ይህ አይነተኛ የአዲስ ኪዳን የትንቢት መጽሐፍ በነብዩ ዳንኤል የትንቢት መጽሐፍ ማጠቃለያ ላይ (ዳን 8፥ 26፤ 12፥ 4) መጽሐፉን በማህተም ዝጋ ከሚለው ጋር የሚገናዘብ ነው። /መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውቀው የፍጻሜ ዘመን ነብዩ ዳንኤል ትንቢቱንና ራእዩን ከተቀበለበትና በነብይነት ካገለገለበት ዘመን አንጻር ገና ብዙ ዘመን ይቀረው ስለነበር ትንቢቱን በማህተም እንዲዘጋው መመርያን ተቀበለ፤ ይኸው አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውቀውና"ዘመኑ" እየተባለ የሚጠራው የመጨረሻው ዘመን ደግሞ ሐዋርያው ዮሐንስ ካገለገለበት ዘመን አንጻር እጅግ የቀረበ ስለነበር የመጽሐፉን ቃል "በማህተም አትዝጋው" የሚልን መመርያ ተቀበለ/።
የራእይ መጽሐፍ ሁነቶች የተጻፉትና የሚፈጸሙት መጽሐፉ ከተጻፈበት ጊዜ አንጻር በብዙ ሺህ አመታት ርቀት ለሚኖሩ ሰዎች ከሆነ፣ ያኔ ገና በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ይኖሩ የነበሩ የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ሰዎች በመጽሐፉ የተገለጠው አውሬው ማን እንደሆነ ሊረዱ ይችላሉ ሲል መጽሐፉ ለምን አጽንኦት ይሰጠዋል? በእስያስ ቢሆን ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ የነበሩበት ትክክለኛው ጊዜ በ60ዎቹ አ.ም መሆኑ ትክክለኛ ታሪክ አይደለም ወይ?
የዮሐንስ ራእይ አብይ መልእክትና ርእሰ ጉዳይ በባቢሎን (ታላቂቱ ከተማ እና ጋለሞታይቱ) ላይ የሚደርሰውን ፍርድ በተመለከተ እንደሆነ በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ዘንድ አጠቃላይ የሆነ መግባባት አለ። እንግዲህ ባቢሎን በሚል ሥያሜ የተጠራችው ከተማ በብዙ አመታት ርቀት ወደ ፊት ገና የምትጠበቅ አይነት ከሆነች፣ ታዲያ የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ራሱ ባቢሎን፣ ታላቂቱ ከተማ፣ "ጌታ የተሰቀለባት" (ራእ 11፥ 8፤ 18፥ 10፣ 19፣ 20፣ 24፤ 19፥ 2) ብሎ በመጥራት ለምን የብሉይ ኪዳንዋን ኢየሩሳሌምን ይገልጣታል?
በብሉይ ኪዳንስ ቢሆን እስራኤል ያልታመነች ሆና በተገለጠችበት ስፍራ ሁሉ "ጋለሞታ" እና "አመንዝራ" በተሰኙ አሳፋሪ ባህርያት ስትጠራ አልነበረምን (ኤር 3፥ 6-9፤ ሕዝ 16፥ 26፣ 28)?
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ላነሳው የሚገባኝ በርካታ ነጥብ ያለ ቢሆንም መደረግ ላለበት ክለሳና የአስተሳስብ ለውጥ መንደርደሪያ እንዲሆነን ለአሁኑ ይህን ያህል ማሰላሰል በቂ ይመስለኛል። ሥራዬ ብለው የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያጠኑ የቃሉ ተማሪዎች ግን በስፋት ሊመለከቱት የሚችሉት አይነት ዝርዝር የጽሁፍ ዝግጅት በእጄ ላይ ያለ መሆኑን መግለጥ እወዳለሁ።
ግዛቸው ከበደ /ቄስ/
ተጻፈ ወርሃ በሚያዝያ 2014
አንካራ ቱርክ
ተጻፈ ወርሃ በሚያዝያ 2014
አንካራ ቱርክ
No comments:
Post a Comment