የራእይ ዳሰሳ ባጭሩ

የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ
አጭር ዳሰሳ
በመጽሐፉ ትርጉም ላይ መደረግ ስላለበት የአስተሳሰብ ለውጥ
ጠቋሚ የሆኑ አንዳንድ ነጥቦች
የራእይን መጽሐፍ ስናጠና ከዘመን አኳያ መመለስ ያለበት መሰረታዊ ጥያቄ፦
መጽሐፉ የሚያወራው ያለ በቂ ጥናት በተለምዶ ሲታሰብና ሲታመን እንደነበረው፣ እኛ ካለንበት ከዚህ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን አንጻር ሲታይ ስለ መጻኢው ማለትም ስለ ወደፊቱ ነው? ወይንስ በተቃራኒው ስለ ኃላፊው? ማለትም በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ተፈጽሞ ስለ አለፈ ጉዳይ፣ ስለ የትኛው ዘመን ነው?
የዚህን መሰረታዊ ጥያቄ መልስ ለመወሰን መመለስ ያለባቸውን ተያያዥ የሆኑ ሌሎች ጥያቄዎች ከራሱ ከመጽሐፉ እያነሳን በራሱ በመጽሐፉ መመለስ ይኖርብናል። ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ሳይጣረስና ሳይጣላ መፈታትና መተርጎም ያለበት በራሱ "በእግዚአብሔር ቃል ብቻ" ነው እንጂ፣ በርካቶች በስብከታቸውና በትምህርታቸው ብሎም በመዝሙራቸው እንደሚያንጸባርቁት በዚህ በአሁኑ የ21ኛው ክፍለ ዘመን አለም፣ በየእለቱ በመገናኛ ብዙሃን በምንሰማውና በጋዜጦች በምናነበው ትኩስ ዜና፣ በመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ውዝግብም ሆነ በየትኛውም ልዕለ ኃያል ሃገርና መንግስት የፖለቲካ ትኩሳት መተርጎም አግባብ አይደለም።
ሌላ ተያያዥ ጥያቄ፣ የራዕይ መጽሐፍ የሚናገረው መጽሐፉ ከተጻፈበት የመጀመርያው ክፍለ ዘመን አንጻር ከረጅም ዘመን በኋላ ምናልባትም ገና ከዚህ ከ21ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ስለሚሆኑ ሁነቶች ነው ከተባለ፣ ታዲያ በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙ በርካታ የንባብ ክፍሎች የሚያነሱአቸው ጉዳዮች ለምን በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ከነበረችው እስራኤል ጋር የሚገናኙ ሁነቶች  ሆኑ?
እነዚህም በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ከነበረችው እስራኤል ጋር የሚገናኙ ሁነቶችን የሚያመለክቱ ከዚህ በታች የተጠቀሱ የንባብ ክፍሎች የተሰጡባቸውን አውድ ለቃሉ ብቻ ታማኝ ሆነን በጥንቃቄ ብንመለከት፣ ትንቢቱ ሲነገርና መጽሐፉ ሲጻፍ የሚፈጸምበትንም የጊዜ ማእቀፍ እያመለከተ የተሰጠ ቃል መሆኑን ጨምረን እናስተውላለን።
በመጽሐፉም ውስጥ በተለይ ልናስተውላቸው የሚገቡንን አራት ነጥቦች ላንሳላችሁ ( እነዚህም ለዚህ አጭር የመግቢያ ጥናት ብቻ በወፍ በረር ላነሳቸው የምፈልጋቸው ነጥቦች ናቸው)፦
(ሀ) በመጽሐፉ ውስጥ በግልጽ የተቀመጡ ጊዜን አመልካች የሆኑ ምንባባት ያሉ መሆናቸውን ልብ በሉና ተመልከቱ፣
(ለ) በግልጽ ተወስኖ ከተሰጠና ጊዜን አመልካች ከሆኑ ከሌሎች የአዲስ ኪዳን ምንባባት ጋር ዝምድና ያላቸው ምንባባት የሚገኙበት መሆኑንም አስተውሉ
(ሐ) በተለይ ጥንታዊዋንና የቀድሞውን ኪዳን ኢየሩሳሌምን ወይም የእስራኤልን ሕዝብ በማመልከት አንጻር የተነገሩ ምንባባት ያሉበት መሆናቸውንም ተመልከቱ፤ እንዲሁም
(መ) የመጀመሪያይቱ ክፍለ ዘመን ኢየሩሳሌም በወቅቱ ከነበረችበት አይነተኛ የአይሁድ ማህበረሰብ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ጋር በራእዩ መጽሐፍ የተገለጡ አይነተኛ ቦታዎችና ዘመኑ የተገናዘቡ መሆናቸውንም ተረዱ።
የሚከተሉትን የንባብ ክፍሎች ከፍ ሲል ከተጠቀሱት 4 ነጥቦች አንጻር መጽሐፍ ቅዱሳችሁን እያመሳከራችሁ በጥንቃቄ ትመለከቱአቸው ዘንድ እጋብዛለሁ፦
ራእይ ምዕራፍ 1 ቁ. 1 "ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥ "
ቁ.3 "ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው። "
ቁ.7 "እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን። "
ቁ.9 "እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ"
ቁ.10 "በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ትላቅ ድምፅ ሰማሁ፥" 
ቁ.19 "እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ"
ራእይ ምዕራፍ 2 ቁ. 10 "ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ። እነሆ፥ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፥ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ። " 
ቁ.16 "እንግዲህ ንስሐ ግባ፤ አለዚያ ፈጥኜ እመጣብሃለሁ፥ በአፌም ሰይፍ እዋጋቸዋለሁ።"
ቁ.25 "ነገር ግን እስክመጣ ድረስ ያላችሁን ጠብቁ።"
ራእይ ምዕራፍ 3 ቁ. 10 "የትዕግሥቴን ቃል ስለ ጠበቅህ እኔ ደግሞ በምድር የሚኖሩትን ይፈትናቸው ዘንድ በዓለም ሁሉ ላይ ሊመጣ ካለው ከፈተናው ሰዓት እጠብቅሃለሁ።"
ቁ .11 "እነሆ፥ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።"
ራእይ ምዕራፍ 4 ቁ. 1 "ከዚያ በኋላም አየሁ፥ እነሆም በሰማይ የተከፈተ ደጅ፥ እንደ መለከትም ሆኖ ሲናገረኝ የሰማሁት ፊተኛው ድምፅ፦ ወደዚህ ውጣና ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚያስፈልገውን ነገር አሳይሃለሁ አለ።"
ራእይ ምዕራፍ 6 ቁ.16-17 "ተራራዎችንና ዓለቶችንም፦ በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን፤ ታላቁ የቁጣው ቀን መጥቶአልና፥ ማንስ ሊቆም ይችላል? አሉአቸው። "
 
ራእይ ምዕራፍ 8 ቁ.13 "አየሁም፥ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ፦ ሊነፉ ያላቸው የሦስቱ መላእክት መለከት ስለሚቀረው ድምፅ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው፥ ወዮላቸው፥ ወዮላቸው ሲል ሰማሁ።"
ራእይ ምዕራፍ 10 ቁ.6-7 "ሰማይንና በእርሱም ያሉትን፥ ምድርንና በእርስዋም ያሉትን፥ ባሕርንና በእርሱም ያሉትን በፈጠረው፥ ከዘላለምም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ሆኖ በሚኖረው ምሎ።  ወደ ፊት አይዘገይም፥ ዳሩ ግን ሰባተኛው መልአክ ሊነፋ ባለው ጊዜ ድምፁም በሚሰማበት ዘመን፥ ለባሪያዎቹ ለነቢያት የምስራች እንደ ሰበከላቸው የእግዚአብሔር ምሥጢር ይፈጸማል አለ። "
ራእይ ምዕራፍ 11 ቁ. 1-2  "በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፥ እንዲህም ተባለልኝ፦ ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ። በመቅደሱም ውጭ ያለው እድሞ ለአሕዛብ ተሰጥቶአልና ተወው አትለካውም፤ እነርሱም አርባ ሁለት ወር የተቀደሰችውን ከተማ ይረግጡአታል።"
ቁ. 8 "በታላቂቱ ከተማ አደባባይ ይተኛል እርስዋም በመንፈሳዊ ምሳሌ ሰዶምና ግብጽ የተባለች ደግሞ ጌታቸው የተሰቀለባት ናት።"
ቁ.15-19 "ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ። በእግዚአብሔርም ፊት በዙፋኖቻቸው የተቀመጡ ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በግምባራቸው ተደፍተው ለእግዚአብሔር እየሰገዱ እንዲህ አሉ፦ ያለህና የነበርህ ሁሉን የምትገዛ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ትልቁን ኃይልህን ስለ ያዝህ ስለ ነገሥህም እናመሰግንሃለን፤  አሕዛብም ተቈጡ፥ ቍጣህም መጣ፥ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፥ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።  በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።"
ራእይ ምዕራፍ 12 ቁ. 5 "አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ።"
ራእይ ምዕራፍ 14 ቁ.7 "በታላቅ ድምፅም፦ የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና እግዚአብሔርን ፍሩ ክብርንም ስጡት፤ ሰማይንና ምድርንም ባሕርንም የውኃንም ምንጮች ለሠራው ስገዱለት አለ። "
ቁ.14-20 "አየሁም፥ እነሆም ነጭ ደመና፥ በደመናውም ላይ የሰውን ልጅ የሚመስል ተቀምጦአል፥ በራሱም ላይ የወርቅ አክሊል በእጁም ስለታም ማጭድ ነበረው። ሌላ መልአክም ከመቅደሱ ወጥቶ በደመናው ላይ ለተቀመጠው፦ የማጨድ ሰዓት ስለ ደረሰ ማጭድህን ስደድና እጨድ፥ የምድሪቱ መከር ጠውልጓልና ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው ምድርም ታጨደች። ሌላ መልአክም በሰማይ ካለው መቅደስ ወጣ፥ እርሱም ደግሞ ስለታም ማጭድ ነበረው። በእሳትም ላይ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከመሠዊያው ወጥቶ ስለታም ማጭድ ያለውን፦ ዘለላዎቹ ፈጽመው በስለዋልና ስለታሙን ማጭድህን ስደድና በምድር ያለውን የወይን ዛፍ ዘለላዎች ቍረጥ ብሎ በታላቅ ድምፅ ጠራ። መልአኩም ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፥ በምድርም ካለው ከወይን ዛፍ ቈርጦ ወደ ታላቁ ወደ እግዚአብሔር ቍጣ መጥመቂያ ጣለ።  የወይኑም መጥመቂያ ከከተማ ውጭ ተረገጠ፥ እስከ ፈረሶች ልጓምም የሚደርስ ደም ርቀቱ ሺህ ስድስት መቶ ምዕራፍ ሆኖ ከመጥመቂያው ወጣ። "
ራእይ ምዕራፍ 15 ቁ 5-8 "ከዚህም በኋላ አየሁ፥ የምስክርም ድንኳን መቅደስ በሰማይ ተከፈተ፥ ሰባቱንም መቅሠፍት የያዙ ሰባቱ መላእክት ከመቅደሱ ወጡ፤ ከተልባ እግርም የተሠራ ጥሩ የጌጥ ልብስ ለበሱ ደረታቸውንም በወርቅ መታጠቂያ ታጠቁ። ከአራቱም እንስሶች አንዱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ የሚኖር የእግዚአብሔር ቍጣ የሞላባቸውን ሰባት የወርቅ ጽዋዎች ለሰባቱ መላእክት ሰጣቸው።  ከእግዚአብሔርም ክብርና ከኃይሉ ጢስ በመቅደሱ ሞላበት፥ የሰባቱ መላእክት ሰባቱ መቅሰፍት እስኪፈጸሙ ድረስ አንድ እንኳ ወደ መቅደሱ ይገባ ዘንድ አልቻለም።"
ራእይ ምዕራፍ 16 ቁ.6 "የነቢያትን ደም ስላፈሰሱ ደምን ደግሞ አጠጥተሃቸዋል፥ የሚገባቸው ነውና ብሎ ሲናገር ሰማሁ።"
ቁ. 19 "ታላቂቱም ከተማ በሦስት ተከፋፈለች፥ የአሕዛብም ከተማዎች ወደቁ። ታላቂቱም ባቢሎን የብርቱ ቍጣው ወይን ጠጅ የሞላበትን ጽዋ እንዲሰጣት በእግዚአብሔር ፊት ታሰበች።"
ራእይ ምዕራፍ 17 ቁ.8 "ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፥ አሁንም የለም፥ ከጥልቁም ይወጣ ዘንድ አለው፥ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ በምድር የሚኖሩ አውሬው አስቀድሞ እንደነበረ አሁንም እንደሌለ፥ ነገር ግን እንዳለ ሲያዩ ያደንቃሉ። "
ራእይ ምዕራፍ 18 ቁ.24 "በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።"
ራእይ ምዕራፍ 20 ቁ. 7-10፣ "ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፥ በአራቱም በምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ፥ ጎግንና ማጎግን፥ እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትታቸው ይወጣል፤ ቍጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው። ወደ ምድርም ስፋት ወጡ የቅዱሳንንም ሰፈርና የተወደደችውን ከተማ ከበቡ፤ እሳትም ከሰማይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወርዳ በላቻቸው። ያሳታቸውም ዲያብሎስ አውሬውና ሐሰተኛው ነቢይ ወዳሉበት ወደ እሳቱና ወደ ዲኑ ባሕር ተጣለ፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ። "
ቁ. 11-15  "ታላቅና ነጭ ዙፋንን በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፥ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ ስፍራም አልተገኘላቸውም። ሙታንንም ታናናሾችንና ታላላቆችን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፥ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ እርሱም የሕይወት መጽሐፍ ነው፤ ሙታንም በመጻሕፍት ተጽፎ እንደ ነበረ እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈሉ።  ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ። ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።  በሕይወትም መጽሐፍ ተጽፎ ያልተገኘው ማንኛውም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣለ። "
ራእይ ምዕራፍ 22 ቁ.6-7 "እርሱም፦ እነዚህ ቃሎች የታመኑና እውነተኛዎች ናቸው፥ የነቢያትም መናፍስት ጌታ አምላክ በቶሎ ሊሆን የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ እንዲያሳይ መልአኩን ሰደደ። እነሆም፥ በቶሎ እመጣለሁ። የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል የሚጠብቅ ብፁዕ ነው አለኝ። "
ቁ. 10 "ለእኔም፦ ዘመኑ ቀርቦአልና የዚህን መጽሐፍ ትንቢት ቃል በማኅተም አትዝጋው።"
ቁ.12፣ "እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።"   ቁ. 20 "ይህን የሚመሰክር፦ አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።"
ከነዚህ ምንባባት መካከል አንዳንዶቹ ጊዜን በማመልከት አንጻር በግልጽ የተቀመጡና ሊሆኑ ያሉትን ሁነቶች የሚያመለክቱ ሲሆኑ እነርሱም "ቶሎ" ወይም ቅርብ ወይም ሳይዘገዩ የሚፈጸሙ ጉዳዮች መሆናቸውን ያሳያሉ። በተጨማሪም ከነዚህ ምንባባት መካከል አንዳንዶቹ በግሪኩ 'mello' የተሰኘውን ቃል ይዘዋል (1፥ 19፤ 3፥ 10፤ 8፥ 13፤ 10፥ 7፤ 22፥ 10፣ 12፣ 20 ተመልከቱ) ይኸውም "ይሆን ዘንድ ያለው"  ("abaut to be") ተብሎ ተተርጉሞአል። ቃሉም አንዳች የሚጠባበቁት ጉዳይ ሳይዘገይና ምንም ጊዜ ሳይወስድ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ሊፈጸም ቀነ ቀጠሮ የተቆረጠለት መሆኑን ያመለክታል።
ይህ ጊዜን አመልካች የሆነው ንግግር በመላው የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ፣ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ፣ በመሐል እና በመጽሐፉ ማጠቃለያ ላይ ተደጋግሞ መጠቀሱ ትንቢቱ አንድ ወጥ ሆኖ ሳይነጣጠልና ሳይከፋፈል በተያዘለት ቀነ ቀጠሮ ይኸውም "ቶሎ"፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተፈጻሚ የሚሆንበትን አይነተኛ ጊዜ የሚያመለክት ነው። ይህም "ቶሎ" የትንቢቱ ተቀባዮች በኩረ ተደራስያኑ ገና በህይወት ሳሉ በትዉልዳቸዉ ውስጥ የሚደርስ ቶሎ ነው እንጂ የዚህ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የእኛ ቶሎ አይደለም። ይኸውም ደግሞ ጌታችን በስጋው ወራት እየደጋገመ ለተከታዮቹ ያስተማራቸውን ፍካሬውን የሚያስተጋባ ንግግር ነው። "እውነት እላችኋለሁ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል"፣ "ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም"፣ "የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ እዚህ ከሚቆሙት ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ"፣ "እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም"፣ "የሰው ልጅ በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ" ...ወዘተ።
ስለዚህ ማንም ቢሆን በዚህ የትንቢት መጽሐፍ ላይ አውድ ዘለል የሆነ ትርጉምን ተከትሎ ስህተትን ሳይፈጽም የነዚህን ሁነቶች ፍጻሜ ሊከፋፍልም ሆነ የትንቢቱን ፍጻሜ ከተጻፈበት የመጀመርያው ክፍለ ዘመን አንጻር በብዙ የዘመን ርቀት አራዝሞ አሁንም ሆነ ወደፊት ሊጠባበቅ አይችልም።
በቀጣዩ ጽሑፌ የራእይ መጽሐፍ ስለተጻፈበት ጊዜ አነሳና ጊዜውን አስመልክቶ ያለው ሙግት በምንከተለው አመለካከት ላይ የሚያሳርፈውን ተጽእኖ ለመዳሰስ እወዳለሁ። ለአሁን በጽሑፍ ርዝመት እንዳንሰለቻች በዚሁ ይብቃን። ቸር ሰንብቱ!
#########
ያለፉና አሁን ያሉ በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት መጽሐፉ ከ70 ዓ.ም በፊት መጻፉንና እንዲሁም የኢየሩሳሌምንና የቤተ መቅደሱን ውድመት ከበው ያሉ ሁነቶችን በተመለከተ የተነገረ መሆኑን ያምናሉ።
የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ገና አሁንም ወደፊት በብዙዎች ሰለሚጠበቀውና መጻኢ ስለሆነው ስለ "መጨረሻው ቀን" የተነገረ ከሆነ፣ ታድያ በአዲስ ኪዳን ውስጥ በብዙ ስፍራ ስለ መጨርሻው ቀኖች የተነገሩ ክፍሎች ለምን በግልጽ የመጀመሪያውን ክፍለ ዘመን ያመለክታሉ? ለምሳሌ ቀጥሎ የቀረቡትን ጥቅሶች አመሳክሩ፦
ሐዋ 2፥ 14-20፤  ነገር ግን ጴጥሮስ ከአሥራ አንዱ ጋር ቆመ፥ ድምፁንም ከፍ አድርጎ እንዲህ ሲል ተናገራቸው፦ አይሁድ በኢየሩሳሌምም የምትኖሩ ሁላችሁ፥ ይህ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፥ ቃሎቼንም አድምጡ። ለእናንተ እንደ መሰላችሁ እነዚህ የሰከሩ አይደሉም፥ ከቀኑ ሦስተኛ ሰዓት ነውና፤ ነገር ግን ይህ በነቢዩ በኢዩኤል የተባለው ነው። እግዚአብሔር ይላል፦ በመጨረሻው ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሥጋ በለበሰ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፥ ጎበዞቻችሁም ራእይ ያያሉ፥ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤ ደግሞም በዚያች ወራት በወንዶችና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ ትንቢትም ይናገራሉ። ድንቆችን በላይ በሰማይ፥ ምልክቶችንም በታች በምድር እሰጣለሁ፤ ደምም እሳትም የጢስ ጭጋግም ይሆናል፤ ታላቅ የሆነ የተሰማም የጌታ ቀን ሳይመጣ ፀሐይ ወደ ጨለማ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።
1ጢሞ 4፥ 1፤   መንፈስ ግን በግልጥ፦ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል፤....
2ጢሞ 3፥ 1፤ ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ።
እብ 1፥ 2፤   ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፤
ያዕ 5፥ 3-9፤  በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል። እንደ አሮንም በእግዚአብሔር ከተጠራ በቀር ማንም ክብሩን ለራሱ የሚወስድ የለም። እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ ሊቀ ካህናት ሊሆን ራሱን አላከበረም ነገር ግን፦ አንተ ልጄ ነህ እኔ ዛሬ ወልጄሃለሁ ያለው እርሱ ነው፤ እንደዚህም በሌላ ስፍራ ደግሞ፦ አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ይላል። እርሱም በስጋው ወራት ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ ተሰማለት፤ ምንም ልጅ ቢሆን፥ ከተቀበለው መከራ መታዘዝን ተማረ፤ ከተፈጸመም በኋላ በእግዚአብሔር እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ሊቀ ካህናት ተብሎ ስለ ተጠራ፥ ለሚታዘዙለት ሁሉ የዘላለም መዳን ምክንያት ሆነላቸው።
1ጴጥ 1፥ 5፣ 20፣ ፤ ...ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።.....ዓለም ሳይፈጠር እንኳ አስቀድሞ ታወቀ፥ ነገር ግን እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሙታን ባስነሣው ክብርንም በሰጠው በእግዚአብሔር በእርሱ ስለምታምኑ ስለ እናንተ በዘመኑ መጨረሻ ተገለጠ።
2ጴጥ 3፥ 3፤  በመጨረሻው ዘመን እንደ ራሳቸው ምኞት የሚመላለሱ ዘባቾች በመዘበት እንዲመጡ ይህን በፊት እወቁ፤
1ዮሐ 2፥ 18፤ ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን
ይሁዳ 18 እነርሱ፦ በመጨረሻው ዘመን በኃጢአተኝነት እንደ ገዛ ምኞታቸው እየሄዱ ዘባቾች ይሆናሉ ብለዋችኋልና።
የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ የያዛቸው ሁነቶች መጽሐፉ ከተጻፈበት ከመጀመርያው ክፍለ ዘመን በዘለለ ከሺህዎች አመታት በኋላ የሚሆኑና የሚፈጸሙ ጉዳዮች ከሆኑ፣ የዮሐንስ በራእዩ ስለ "ስድስተኛው ንጉስ" በተናገረ ጊዜ ለምን "አንዱም አለ" ሲል ይናገራል?
ራእ 17፥ 10 "ሰባት ነገሥታት ደግሞ ናቸው፤ አምስቱ ወድቀዋል አንዱም አለ፥ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል።"
ራዕዩ በተለይ ስለ ሰባት ነገስታት ጠቅሶ ይናገራል፡፡ "አምስቱ ወድቀዋል" የተባሉት፣ ይኸውም ራዕዩ ከመሰጠቱና ከመጻፉ በፊት ተፈራርቀው የነገሱት ነገስታት ናቸው፡፡ "አንዱም አለ"፣ ይህ በአሁን ጊዜ አመልካች ንግግር የተጠቀሰውና "አለ" የተባለው ራዕዩ ሲጻፍና ሲሰጥ ይገዛ የነበረው ንጉስ ነው፡፡ ሰባተኛው ገና አልመጣም ሲመጣም ብዙ አይቆይም የተባለው ነው፣ እርሱም ከራዕዩ መሰጠትና መጻፍ በኋላ የሚመጣ ነው፡፡
ዮሐንስ በራእዩ ምዕራፍ 14፥ 7 ላይ "የፍርዱ ሰዓት ደርሶአልና" ብሎ ሲናገር፣ እርሱ ከነበረበት ጊዜ በብዙ ርቀት ገና ወደፊት ስለሚመጣ ጊዜ ሊያመለክት እንዴት ይቻለዋል?
144,000ዎቹ (ራእ 7፥ 14) ከሺህዎች አመታት በኋላ ስለሚታተሙ ሰዎች የተነገረ ከሆነ, ታድያ የንባብ ክፍሉ በኩራት ናቸው ሲል ለምን ይናገራል?
መከራውስ ቢሆን ዮሐንስ ከነበረበት ጊዜ አንጻር ገና ወደፊት ያለና የሚጠበቅ ነገር ከሆነ፣ ታድያ ራእዩን እየጻፈ በነበረበት ጊዜ ያኔውኑ እርሱ ራሱም ቢሆን በመከራው ውስጥ እንደነበር ለምን ይናገራል (ራእ 1፥ 9)?
የራእዩ መጽሐፍ ሁነቶች የሚፈጸሙት ከተጻፉበት ጊዜ አንጻር ገና ወደ ፊት ብዙ ዘመን ቆይተው ከሆነ ታዲያ ዘመኑ ቀርቦአልና የመጽሐፉን ቃል በማህተም አትዝጋው የሚልን መመርያ ለምን ተቀበለ (ራእ 22፥ 10)?
ይህ አይነተኛ የአዲስ ኪዳን የትንቢት መጽሐፍ በነብዩ ዳንኤል የትንቢት መጽሐፍ ማጠቃለያ ላይ (ዳን 8፥ 26፤ 12፥ 4) መጽሐፉን በማህተም ዝጋ ከሚለው ጋር የሚገናዘብ ነው። /መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውቀው የፍጻሜ ዘመን ነብዩ ዳንኤል ትንቢቱንና ራእዩን ከተቀበለበትና በነብይነት ካገለገለበት ዘመን አንጻር ገና ብዙ ዘመን ይቀረው ስለነበር ትንቢቱን በማህተም እንዲዘጋው መመርያን ተቀበለ፤ ይኸው አንዱ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያውቀውና"ዘመኑ" እየተባለ የሚጠራው የመጨረሻው ዘመን ደግሞ ሐዋርያው ዮሐንስ ካገለገለበት ዘመን አንጻር እጅግ የቀረበ ስለነበር  የመጽሐፉን ቃል "በማህተም አትዝጋው" የሚልን መመርያ ተቀበለ/።
የራእይ መጽሐፍ ሁነቶች የተጻፉትና የሚፈጸሙት መጽሐፉ ከተጻፈበት ጊዜ አንጻር በብዙ ሺህ አመታት ርቀት ለሚኖሩ ሰዎች ከሆነ፣ ያኔ ገና በመጀመርያው ክፍለ ዘመን ላይ ይኖሩ የነበሩ የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ሰዎች በመጽሐፉ የተገለጠው አውሬው ማን እንደሆነ ሊረዱ ይችላሉ ሲል መጽሐፉ ለምን አጽንኦት ይሰጠዋል? በእስያስ ቢሆን ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ብቻ የነበሩበት ትክክለኛው ጊዜ በ60ዎቹ አ.ም መሆኑ ትክክለኛ ታሪክ አይደለም ወይ?
የዮሐንስ ራእይ አብይ መልእክትና ርእሰ ጉዳይ በባቢሎን (ታላቂቱ ከተማ እና ጋለሞታይቱ) ላይ የሚደርሰውን ፍርድ በተመለከተ እንደሆነ በበርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ዘንድ አጠቃላይ የሆነ መግባባት አለ። እንግዲህ ባቢሎን በሚል ሥያሜ የተጠራችው ከተማ በብዙ አመታት ርቀት ወደ ፊት ገና የምትጠበቅ አይነት ከሆነች፣ ታዲያ የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ ራሱ ባቢሎን፣ ታላቂቱ ከተማ፣ "ጌታ የተሰቀለባት" (ራእ 11፥ 8፤ 18፥ 10፣ 19፣ 20፣ 24፤ 19፥ 2) ብሎ በመጥራት ለምን የብሉይ ኪዳንዋን ኢየሩሳሌምን ይገልጣታል?
በብሉይ ኪዳንስ ቢሆን እስራኤል ያልታመነች ሆና በተገለጠችበት ስፍራ ሁሉ "ጋለሞታ" እና "አመንዝራ" በተሰኙ አሳፋሪ ባህርያት ስትጠራ አልነበረምን (ኤር 3፥ 6-9፤ ሕዝ 16፥ 26፣ 28)?
በዚህ ርእሰ ጉዳይ ላይ ላነሳው የሚገባኝ በርካታ ነጥብ ያለ ቢሆንም መደረግ ላለበት ክለሳና የአስተሳስብ ለውጥ መንደርደሪያ እንዲሆነን ለአሁኑ ይህን ያህል ማሰላሰል  በቂ ይመስለኛል። ሥራዬ ብለው የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያጠኑ የቃሉ ተማሪዎች ግን በስፋት ሊመለከቱት የሚችሉት አይነት ዝርዝር የጽሁፍ ዝግጅት በእጄ ላይ ያለ መሆኑን መግለጥ እወዳለሁ።
ግዛቸው ከበደ /ቄስ/
ተጻፈ ወርሃ በሚያዝያ 2014
አንካራ ቱርክ
    
ጥቂት ስለ የዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ

የሙታን ትንሣኤ መግባቢያ 1እና 2

@ "M/D/YYYY"12/27/2016.
አስተምህሮተ ትንሳኤ "የሚሻል ትንሳኤ" መግባብያ ፩

አካላዊ ትንሣኤን (በሥጋ መነሳትን) በተመለከተ የሚናገሩ ምንባባት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸው በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት አለው፣ እነዚህም ምንባባት ከጥቂቶቹ በቀር በዋናነት የራሱን የኢየሱስ ባዮሎጂካል ትንሳኤ የሚያመለክቱ ናቸው። ሆኖም ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አካላዊ ያልሆነን የትንሳኤ ተፈጥሮን የሚያመለክቱ በርካታ ምንባባት ያሉ መሆናቸው ደግሞ አግራሞትን ይፈጥራል። ይህ አይነቱ የትንሳኤ አይነት ደግሞ፣ የሙታን ትንሳኤ ማለት የሙታን በድኖች ከምድር ጉድጓድ ከመቃብራቸው ውስጥ ወጥተው የሚመጡበት አይነት ብቻ እንዳልሆነ ግንዛቤን ያጭራል።

ይህ አይነቱ የትንሳኤ ተፈጥሮ በኃጢአት ከሚሆን መንፈሳዊ ሙትነት ወደ አዲሱ ኪዳን መንግስት የዘላለም ሕይወት የሚያሻግር ትንሳኤ ነው። እነዚህም ትንሳኤ ተኮር የሆኑ ምንባባት አካላዊ ትንሳኤን በተመለከተ ከተነገሩት ይልቅ በቁጥር እጅግ የሚበዙ መሆናቸው ጠያቂ ለሆነ ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ አማኝና ተማሪ ቀላል ግምት የማይሰጣቸው ናቸው። እንደ እውነቱ ከሆነ ከምድር ጉድጓድ ከመቃብር ውስጥ የሚወጣ አካላዊ ትንሳኤን የማያምኑና የማያስተምሩ በርካታ የመጻኢነት ነገረ ፍጻሜን የሚከተሉ ተርጓሚዎች እንኳ እንዳሉ ብዙዎች አይገነዘቡም። ስለዚህ የተለየውን አይነት ትንሳኤ የሚያስተምሩ ኃላፋውያን ብቻ አይደሉም ማለት ነው።

አካላዊ የሆነው የኢየሱስ ትንሳኤ በዋናነት "ሥጋው መበስበስን እንዳያይ" (ሐዋ 2፥ 27) ለእርሱ ለቅዱሱ ብቻ የተገባለትን የተስፋ ቃል ፍጻሜ የሚሰጥ ኃይለኛና ብርቱ ስራ (ኤፌ 1፥ 19-21) የሆነውን ያህል፣ የኢየሱስ ከሆነው ከአካላዊው ትንሳኤ ባልተናነሰ ደግሞ ኃይለኛና ብርቱ እንደሆነ የተነገረለት ሌላ የነገረ ፍጻሜአዊ ትንሳኤ /Eschatological Resurrection/ አይነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በግልጽ ይገኛል።

ለጥናታችን እንደ መግቢያ ይሆነን ዘንድ በሁለት ቀዳሚ ክፍሎች በምንመለከተው በዚህ የመግባቢያ ጥናት በቀላሉ የተወሰኑ ጥቅሶችን እያነሳን እንወያያለን። ለሚነሱት የጥናት መምሪያ ቀላል ሃሳቦች በምክንያታዊነት ጨዋነትን ለተላበሰ ውይይት ክፍት ሆኖ መቅረብና ቃሉን ብቻ ያማከለ ትጋት ወደሚፈለገው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድምዳሜ ያደርሳል የሚልም ተስፋ አለኝ።

ክፍል 1
1ኛ/    እብራውያን 11፥ 35 " ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤" ሲል ይነግረናል

እነዚህ ሴቶች በዘመናቸው አካላዊ ትንሳኤን መስክረዋል። ይህም  እውነት ነው ምንም ጥርጥር የለውም። "ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤" በብሉይ ኪዳን ቢያንስ ሁለት ሴቶች አሉ ሙታኖቻቸውን እንደገና በትንሳኤ የተቀበሉ። ኤልያስ ልጅ የሞተባትን የሰራፕታዋን ባልቴት ልጅዋን ከሞት አስነስቶላታል (1ነገስት 17፥ 17-24)። ኤልሳዕም ልጅ የሞተባትን የሱናማዊቱን ሴት ልጅዋን ከሞት አስነስቶላታል (2ነገስት 4፥ 18-37)። የነብያቱ እምነትና አገልግሎት እነዚህን ልጆች ከሞት መልሶአቸዋል። በአዲስ ኪዳንም ኢየሱስ ማርታ እና ማርያም ለተሰኙ እህትማማቾች ወንድማቸውን አልአዛርን (ዮሐንስ 11፥ 43-44)፣  ከናይን ከተማ ለነበረችው መበለት አንድ ልጅዋን (ሉቃስ 7፥ 13-15)፣  ከሞት አስነስቶላቸዋል። ጳውሎስ ግን ለእብራውያን ክርስቲያኖች "የሚበልጠውን ትንሣኤ" ብሎ በሚጽፍበት ጊዜ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ "ይህ ትንሳኤ ከየትኛው ትንሳኤ የሚበልጥ ነው?" የሚል ነው። መልሱም እነዚህ ሴቶች ከተለማመዱትና በነብያቱ አገልግሎት በልጆቻቸውና በሚወድዱአቸው ላይ ሲፈጸም ካዩት አካላዊ ወይም ባዮሎጂካል ከሆነውና ጊዜአዊ ከሆነው የትንሳኤ አይነት ነው። ታዲያ ከዚህ አይነቱ የሚበልጠው ትንሳኤ የትኛው ትንሳኤ ነው? በግልጽ ቋንቋ ለመናገር እንዲህ ካለው ትንሳኤ የሚበልጠው ትንሳኤ የአካላዊውና የተዳሳሹ ትንሳኤ ተቃራኒ መንፈሳዊና ዘላለማዊ የሆነው ትንሳኤ ነው፤ ይኸውም ሰው ከፈጣሪው ጋር በሰማያዊው አገር ዘላለማዊ በሆነው እርቅና ህብረት የሚደሰትበት የእግዚአብሔር ሕይወት ነው።

የሆነው ሆኖ ልክ እንደነዚሁ ሴቶች...... ሌሎች ደግሞ የሚበልጠውን ትንሳኤ እንዲያገኙ ተስፋ አድርገዋል። ይህም እውነት ነው።

ይህ ጥቅስ የሚነግረን አንድ እውነት አለ፣ ይኸውም እነዚያ የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በሆነ አይነት የትንሳኤ ተስፋ ያምኑ እንደ ነበር ነው፤ ይሄ ደግሞ ከዚያ የሚበልጥና የሚሻል እንጂ የግድ አካላዊ (ጊዜአዊ) መሆን አያስፈልገውም። ለምሳሌ፦ ማርታ እንደዚያ ታምን ነበር፤ ኢየሱስ "ወንድምሽ ይነሳል" ባላት ጊዜ "በመጨረሻው ቀን በትንሳኤ እንዲነሳ አውቃለሁ" ( ዮሐ 11፥ 23-24) ከሚለው መልስዋ የምንረዳው በአይሁድ ዘንድ ይታመን ስለነበረው የትንሳኤ አይነት ነው።

ይህንን "የሚበልጥ" ወይም "የሚሻል" የተሰኘ ቁልፍ ቃል በመላው የእብራውያን መልእክት ውስጥ ያለውን ቦታ ልብ በሉ፤ ለአዲስ ኪዳን በረከቶችና ትሩፋት ሁሉ መግለጫ የሆነ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከተገለጡና ጉድለት ካለባቸው የህጉና የስጋ ከሆኑ ነገሮች ሁሉ የአዲስ ኪዳኑን ስጦታ ከፍ አድርጎ የሚለይ ቃል ነው። "የሚበልጥ" ወይም "የሚሻል" በተሰኘ ደረጃ በእብራውያን መልእክት ውስጥ የተገለጡ የአዲሱ ኪዳን ስጦታዎች በሙሉ ደግሞ በክርስቶስ የተገኙና የተያዙ ነገሮች እንጂ ገና በብዙ ዘመን ርቀት የሚጠበቁ መጻኢ ተስፋዎች አልነበሩም፤ ለምሳሌ፣ የሚበልጥ ሊቀካህን፣ የሚበልጥ ኪዳን፣ የሚበልጥ መስዋእት፣ የሚሻል አገልግሎት ወዘተ። "የሚበልጥ ትንሳኤ" ኢየሱስ የእኛ ብልጫ! ለማርታ እንዲህ ሲል የሚበልጠውን ትንሳኤ አረጋግጦላታል "ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም"
2ኛ/ ዘፍጥረት 2፥ 16-17 " እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።"  የሚል ቃል እናነባለን፤

እግዚአብሔር አዳምን ከእውቀት ዛፍ እንዳይበላ ከልክሎታል። ይህም እውነት ነው። እግዚአብሔር ያስጠነቀቀው በበላህ ቀን "ሞትን ትሞታለህ"  ብሎ ነው። ይህም የእግዚአብሔር እውነት ነው። የዲያብሎስ ውሸት ግን "ሞትን አትሞቱም"  የሚል ነበር።
3ኛ/ ዘፍጥረት 3፥ 6 " ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነ፥ ለዓይንም እንደሚያስጎመጅ፥ ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።" ይላል፤

አዳም እግዚአብሔርን ያልታዘዘው ከተከለከለው የዛፍ ፍሬ በመብላት ነው። ሔዋንም ደግሞ ከዛፉ ፍሬ ከባልዋ ጋር አብራ የበላች እስከሆነ ድረስ ሁለቱም በፈጸሙት ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት እኩል ጥፋተኞችና ለሞት ተጠያቂዎች ናቸው።

4ኛ/ ዘፍጥረት። 3፥ 22 - 4፥2ሀ "እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔድን ገነት አስወጣው፥ የተገኘባትን መሬት ያርስ ዘንድ። አዳምንም አስወጣው፥ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።  አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ፤ ፀነሰችም፥ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም፦ ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች ደግሞም ወንድሙን አቤልን ወለደች።" የሚል ቃል እናነባለን፤

አዳምና ሔዋን የተከለከለውን የዛፍ ፍሬ በበሉበት በዚያው ቀን አካላዊ ሞትን እንዳልሞቱ እናውቃለን። ነገር ግን.... አዳምና ሔዋን ያኔውኑ ከእግዚአብሔር ፊት ከህልዎቱ ተነጥለዋል፣ (3፥ 8 ጀምሮ ተመልከቱ) ይህ ነው የሞቱት ሞት እውነቱ፣ በጠላትነት መለየት።
የተከለከለውን የዛፍ የፍሬ በበሉ ቀን ኃጢአትን የሰሩ እስከሆነ ድረስ (ኃጢአት ህግን መተላለፍ መሆኑን አትርሱ [1ዮሐንስ 3፥ 4 ተመልከቱ]) በዚያው ቀን ደግሞ አካላዊ ሞትን ባይሞቱም፤ በዚያው ቀን ግን ከእግዚአብሔር ፊት ክህልዎቱ ተነጥለው እንዲወጡ ተደርገዋል፣ ሰለዚህ በኃጢአታቸው ምክንያት የመጣባቸው መዘዝ ሆኖ በዚያኑ ቀን የሞቱት ሞት መንፈሳዊ ሞት እንጂ ስጋዊ/አካላዊ ሞት አልነበረም። በኢሳይያስ 59፥ 2 ያለውን ተመልከቱ፦  ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች፥ እንዳይሰማም ኃጢአታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል። ይኼ ነው የሕይወት ትንሳኤ የሚያስፈልገው የዘላለም ሞት።

5ኛ/ ያዕቆብ። 1፥ 15 "ኃጢአትም...... ሞትን ትወልዳለች።" ይላል። በሮሜ 6፥ 16 ደግሞ ጳውሎስ "ለመታዘዝ ባሪያዎች እንድትሆኑ ራሳችሁን ለምታቀርቡለት፥ ለእርሱ ለምትታዘዙለት ባሪያዎች እንደ ሆናችሁ አታውቁምን?" ሲል ይጠይቅና "ወይም ለሞት የኃጢአት ባሪያዎች ወይም ለጽድቅ የመታዘዝ ባሪያዎች ናችሁ።" ሲል ይመልሳል፤ በ6፥ 23 ላይም የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።" ብሎ ይናገራል። ከዚያም በ7፥ 13 ላይ  "ኃጢአትም...... ለእኔ ሞትን ይሠራ ነበር።" ሲል የናገራል። በመጨረሻም በ7፥ 24 ላይ " ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" ሲል ይጮሃል።

ኃጢአት የሞት ውጤት አለው፤ ስለዚህም ኃጢአት በጳውሎስ ውስጥ ሞትን አስከትሎአል። እውነቱ ይህ ነው። ጳውሎስ ከዚህ ሞት የሚያድነውን ፈልጎ ገና እየጮኸ ባለበት ጊዜ እንኳን በስጋው በህይወት ነበር።
ሰለዚህ ይህ "ሞት" - ማለትም ይህ "መንፈሳዊ የሆነ መለየት"፣ ይኸውም "ከእግዚአብሔር ሕይወት መለየት" የተባለው ሞት (ሞት ማለት "መለየት" ማለት ነው፤ የመዝገበ ቃላትን ፍቺና ኢሳይያስ 59፥ 2 ያለውን ተመልከቱ) ቀጥተኛው የኃጢአት ውጤት ነው፣ እርሱም ገና በስጋ በሕይወት እያለንና እንዲሁም ስጋዊውን ሞት ከሞትንም በኋላ ልንለማመደው የምንችለው ሞት ነው።

"ሙታንን ተዉአቸው ሙታናቸውን ይቅበሩ"  ያለእግዚአብሔር ሕይወት፣ ሟችም ቀባሪም  ያው ተሰብስበው ሁሉም ሙታን ናቸው። ይህ ነው እውነቱ።
ቀጥተኛ የሆነውና ወዲያውኑ የሚመጣው የኃጢአት ውጤት የሆነው ሞት (ይኸውም ኃጢአት እንደ አዳምና ሔዋን ሁሉ እኛም ገና በስጋችን እየኖርን ሳለን የፈጸምነው ነው)፣ በእውነትም "የሞት ኃጢአት" ወይም "የኃጢአት ሞት" ወደ መሆን ይለወጣል። እግዚአብሔር በውድ ልጁ ሞት የሻረውንና መፍትሔ የሰጠውን የሞትን አይነት ተፈጥሮና ምንነቱን በቅጡ ያላወቀ ማንም ሰው ቢሆን የሙታንን ትንሳኤ ተፈጥሮና ምንነት ጊዜውንም ጭምር የማያውቅ ይሆናል።

6ኛ/  1ቆሮንቶስ 15፥ 21-22 "ሞት በሰው በኩል ስለ መጣ ትንሣኤ ሙታን በሰው በኩል ሆኖአልና። ሁሉ በአዳም እንደሚሞቱ እንዲሁ ሁሉ በክርስቶስ ደግሞ ሕያዋን ይሆናሉና።" ሲል ጳውሎስ ይነግረናል። ከዚያም በቁጥር 56 እና 57 ላይ " የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፤  ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ድል መንሣትን ለሚሰጠን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።" ሲል ይጽፋል።
አዳም ሞትን  እንዳመጣብን ሁሉ ፣ ኢየሱስም እንዲሁ  ሕይወትን አመጣልን። ይህ ነው የወንጌል እውነት። በአዳም ጦስ መዘዝ ሆኖ የመጣው ሞት 'የኃጢአት ሞት' ወይም 'የሞት ኃጢአት' ነው። በ "አዳም" ከሆነውና ከተገኘው ሞት (በማንኛውም ሞት ውስጥ እንደሚሆነው ሁሉ) ድኖ እንደገና በሕይወት መኖር የሚቻለው በትንሳኤ አማካኝነት ብቻ ነው - ይኸውም በ"ክርስቶስ" የሚገኝ 'የትንሳኤ ሕይወት' ወይም 'የሕይወት ትንሳኤ' ነው።

ሰለዚህ....... ያሉት ሁለት አካላት ናቸው፣ እነርሱም፦ የሞት ወይም የአዳም አካል (ሮሜ 7፥24) እና የሕይወት ወይም የክርስቶስ አካል (ዮሐንስ 1፥4) ናቸው። ጳውሎስ እንዲህ ይላል፣ "እንዲሁ ደግሞ፦ ፊተኛው ሰው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ ተብሎ ተጽፎአል፤ ኋለኛው አዳም ሕይወትን የሚሰጥ መንፈስ ሆነ።"  ስለዚህ በአንድ ወቅት ያጣነውን መንፈሳዊ ሕይወት መልሶ የሚሰጠውንና የሚመሰርተውን የእግዚአብሔርን አሰራር በአጭሩ አብራርተን እንመልከት።

7ኛ/ ቆላስይስ 3 ፥ 13ሀ ላይ "እናንተም በበደላችሁ... ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ፤ በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ፤" የሚል እናነባለን። እንደዚሁም ኤፌሶን 2፥ 1 እና 5 " በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ " ይልና፣ "በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥"  ሲል ይናገራል። ሰለዚህ ይህንን ከኃጢአት መዳንን አስመልክቶ ጳውሎስ በቁጥር 8 ሀ ላይ " ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ " ሲል ይጽፋል።

እነዚህ ቅዱሳን ጳውሎስ መልእክቱን በጻፈላቸው ጊዜ ገና በስጋ አልሞቱም ነበር፣ አካላዊ ከሆነው ሞትም ደግሞ ገና አልተነሱም ነበር። ይህ ፊት ለፊት ያለው እውነት ነው። ሰለዚህ....... እነዚህ ቅዱሳን በግልጽ እንደሚታወቀው (ኃጢአትን በተመለከተ) የሞቱ ነበሩ (ከእግዚአብሔር  ተለይተው ነበሩ)፣ ነገር ግን (ከእግዚአብሔር ልጅ የተነሳ)  ከእግዚአብሔር ጋር (ሕብረት በማድረግ) አንድ ለመሆን በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ከሞት ተነስተው ነበር። ይህም የተሃድሶ ስራ የተፈጸመው የእግዚአብሔር ልጅ በፈጸመው የመስቀል ስራ ላይ ባላቸው እምነት ነው
 
ኢየሱስ ለአማኞች "ትንሳኤና ሕይወት እኔ ነኝ" (ዮሐንስ 11፥ 25) አላቸው እንጂ፣ ትንሳኤ ከመሬት ውስጥ ቡልቅ ብሎ መውጣት ነው አላለም፤ "የሚያምንብኝም ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤ ሕያው የሆነም የሚያምንብኝም ሁሉ ለዘላለም አይሞትም" (ዮሐንስ 11፥26) አለ እንጂ  መቃብርን አያይም አላለም። እንደውም ሳይሞቱ ተለውጦ በአየር ላይ እየተንሳፈፉ ወደ ሰማይ መብረርንም የሚናፍቁ የንጥቀት ተስፈኞች አይጠፉም፣ (ንጥቀትንና ትምህርቱ የተሰኘውን ጽሁፍ ጨምራችሁ በዚሁ ገጽ ላይ እንድታዩት እመክራለሁ)። "ከሰማይ ከወረደው በቀር ወደ ሰማይ የወጣም" ሆነ የሚወጣ "ማንም የለም፣ እርሱም የሰው ልጅ ነው"። በእውነት ሁላችንም "ትንሳኤና ሕይወት" በሆነው በኢየሱስ ያመንን ሕያዋን ሆነን የብጽዕናን ሞት እንሞታለን፣ ብንሞትም እንኳ በዮሐንስ ራዕይ 14፥ 13 "ከእንግዲህ ወዲህ በጌታ የሚሞቱ ሙታን ብፁዓን ናቸው። .... አዎን፥ ከድካማቸው ያርፉ ዘንድ፥ ሥራቸውም ይከተላቸዋል" ተብሎ እንደ ተጻፈ ለዘላለምም በብጽእናና በትንሳኤ እንኖራለን።

ከእንግዲህ ወዲህ እኛ ያመንን በጌታ እንሞታለን እንጂ በኃጢአት አንሞትም። ሕያው ከሆነው ከኢየሱስም የተነሳ ለዘላለም ሕያዋን ነንና። ሕያዋንም ሆነን "ስሞት ወደ ጌታ እሄዳለሁ" በሚል ዝማሬ  በብጽእና  ስንበት ሕያዋንን ወደ ጌታችን እየሸኘን በብጽዕና የሞታችንን ጊዜ የምንጠብቅ ሕያዋን ነን እንጂ ሙታናችንን የምንቀብር ሙታን አይደለንም። መቼም ቢሆን ቤተክርስቲያን አባሎችዋን በሞት የምርት አትሆ።

ትንሳኤ በዋዛ የሚታይ ቀላል ጉዳይ አይደለም። የመጽሐፍ ቅዱስና የክርስትና አንዱና መሰረታዊ እውነት ሆኖ ኖሮአል ይኖራልም (እብ 6፥ 2)። እግዚአብሔርም ደግሞ የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አምላክ አይደለም፦

"በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም   ስለ ትንሣኤ ሙታን ግን፦ እኔ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ የሚል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ እናንተ የተባለውን አላነበባችሁምን? የሕያዋን አምላክ ነው እንጂ የሙታን አይደለም።" (ማቴዎስ 22፥ 30-32)።

ጳውሎስ በ1ኛ ቆሮንቶስ 15፥ 19 ላይ  "በዚች ሕይወት ብቻ ክርስቶስን ተስፋ ያደረግን ከሆነ፥ ከሰው ሁሉ ይልቅ ምስኪኖች ነን።" ሲል እንደተናገረው፣ በእውነት ትንሳኤ የሚባል ነገር ከሌለ ክርስትናም ዋጋ የሌለው የምድር ላይ ምስኪኖች ተራ ሃይማኖት ብቻ ሆኖ ይቀራል።

ምእመናን ልብ አድርጉ፣ ኤፌሶን 2፥ 4-5 "ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥" ሲል እንደሚያረጋግጠው፤ እኛ እንደሆነ እንዴውኑ ከሞት ተነስተን ወደ ህይወት መጥተናል። ክርስትና የመነሳት ሕይወት ነው። የሚበልጠው ትንሳኤ በበደላችን ሙታን ከነበርንበት ሙትነት ወጥተን ከክርስቶስ ጋር የተሰጠን መዳንና የኃጢአት በይቅርታ የሞላበት የራሱ የክርስቶስ ሕይወት ማለትም ክርስትናችን ካልሆነ በቀር ወደ ፊት ገና የምንቀበለው ሌላ ነገር እንደሆነ እናስብ ዘንድ መጽሐፍ ቅዱስ አይፈቅድልንም።

አሁን በመንፈስ ከሞት ተነስተን በሕይወት አለን! ሞት አሁን ለኛ ለዳንን ሰዎች  አሳሳቢ ጉዳይ አይደለም። ሁላችንም አንድ ቀን በስጋ እንሞታለን፣ ይህም ተፈጥሮአዊ ሕግ ተፈጥሮአዊ ሞት ነው፤ ያ በሚሆንበት ጊዜ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ወዳለን ወደማይገደበውና ወደማይበላሸው ማለቂያም ወደሌለው ዘላለማዊ ህብረት  ወደ ሰማያዊውና መንፈሳዊው አለም በቀላሉ እንሸጋገራለን፤ ደግመንም አንሞትም።

ነገር ግን ወደ ፊት ይሆናል ተብሎ በብዙዎች በሚጠበቀው "የስጋ ትንሳኤ" ተብዬ ተስፋ ገና እሁንም የምትኖሩ ከሆነ፣ በእውነት ያሳዝናል፤ የመዳናችሁን ትርጉምና በቅዱስ ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር ለአዲስ ሕይወት የመነሳታችሁን መንፈሳዊውንና ዘላለማዊውን እውነታ ስታችሁታል ማለት ነው።
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦

አስተምህሮተ ትንሳኤ "የሚሻል ትንሳኤ" መግባብያ ፪
ክፍል 2

በመጀመሪያው ክፍል ጥናታችን እብራውያን 11፥ 35 ላይ "ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤"" የሚለውን ቃል መሰረት አድርገን "የሚሻል ትንሳኤ" በተሰኘው ርዕሰ ጉዳይ ላይ በጥቂቱ ተነጋግረናል፤ ነገር ግን በዚህ ጉዳይ ላይ ይህ አረፍተ ነገር የሐዋርያው ጳውሎስ የመጨረሻው ቃል አይደለም፤ ከቁጥር 39- 40 ስለ ብሉይ ኪዳን ቅዱሳን "እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።" የሚለውን የንባብ ክፍል አክለን በዚህኛው  የጥናታችን ክፍል እንቀጥላለን።

በዚህ ነጥብ ላይ ብዙ ጊዜ ማባከን ሳያስፈልገን "የሚበልጥ" ወይም "የሚሻል" እና "ፍጹም" በሚል ገላጭና ቁልፍ ቃላት፣ (ይህም ቁልፍ ቃል በመላው የእብራውያን መልእክት ውስጥ ያለውን ቦታ ቀደም ሲል አንስተናል) በዚህም ላይ የተነገረው ሃሳብ የሚያመለክተው ያው በቁጥር 35 ላይ "የሚበልጠውን ትንሣኤ" ተብሎ የተነገረለትን ነው፣ ያንን ግልጽ የሆነ የጋራ ስሜት ታሳቢ አድርጌ ወደ ፊት ልገስግስ)
1ኛ/ በዘፍጥረት 3፥19 እግዚአብሔር ለአዳም " ወደ ወጣህበት መሬት እስክትመለስ ድረስ በፊትህ ወዝ እንጀራን ትበላለህ፤ አፈር ነህና፥ ወደ አፈርም ትመለሳለህና" አለው። በኋላም በመዝሙር 103፥ 14 ላይ ዳዊት ስለ እግዚአብሔር ሲናገር፦ "ፍጥረታችንን እርሱ ያውቃልና፤ አቤቱ፥ እኛ አፈር እንደ ሆንን አስብ።" ብሎአል። በ2ኛ ቆሮንቶስ 4፥ 7 ላይም ጳውሎስ ስለ ስጋው ወይም  አካሉ ሲናገር "የሸክላ ዕቃ"  እንደሆነ ይነግረናል። ሰለዚህ.... የአዳም ስጋ ወይም የአካሉ ምንጭና የመጨረሻ እጣ ፈንታ ያው የምድር አፈር ነው። ይህ እውነተኛ የቃሉ ምስክርነት ነው። ልክ እንደዚሁ የሁሉም ሰው ስጋ ምንጩና የመጨረሻ እጣ ፈንታው ደግሞ አሁንም ያው የምድር አፈር ነው።

እነዚህ ምንባባት ተዳሳሽና ተጨባጭ ስለሆነው (ፍጥረታዊውና ውጫዊው) የማንነታችን ክፍል የመጨረሻ እጣ ፈንታ በተመለከተ ምንም ጥርጣሬ አይታይባቸውም። ያው ወደ አፈር መመለስ ብቻ ነው። ነገር ግን ተዳሳሽ ስላልሆነው (መንፈሳዊውና ውስጣዊው) የማንነታችንን ክፍል የመጨረሻ እጣ ፈንታ በተመለከተስ ቃሉ ምን ያስተምራል?

በእውነቱ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህንን የመጨረሻ እጣ ፈንታ የሚገልጠውን የቦታ ስያሜ፣ በእብራይስጡ "ሼኦል"፣ በግሪኩ ደግሞ "ሃደስ" የተሰኙትን ቃላት በቀጥታ እንዳለ ከመውሰድ ይልቅ፤ በትርምና የቃላት ፍቺ ችግር ውስጥ ገብተው፣ ሼኦልን 31 ጊዜ "መቃብር"፣  3 ጊዜ ደግሞ "ጥልቁ" ብለው ተርጉመውታል፣ ሃደስን ደግሞ "ሲኦል" ሲሉ ለ11 ጊዜ ያህል ተርጉመውታል። በ1ኛ ቆሮንቶስ 15፥ 55 ላይ ደግሞ ለብቻው ለየት ባለ አቀራረብ "መቃብር" ተብሎ መተርጎሙ ግራ የሚያጋባ ነው። እነዚህን ስያሜዎች ግን ለምን እንዲህ በቀላሉ መተርጎም አስፈለገ? ምናልባት ምንም ሊያደርጉ ባለመቻላቸውና የትርጉም ሕጸጽ የሚያስከትለውን የመረዳት ችግር በሆነ ምክንያት ሳያስተውሉት ቀርተው ሊሆን ይችላል። ሲኦል በዚህ ጥናት ዘርዘር ተደርጎ ኋላ ላይ ይዳሰሳል። እዚህ ላይ ግን መጠነኛ ነገር ማንሳት ግድ ይላል፦

2ኛ/ መዝሙር 49፥ 15 ዘማሪው (ምናልባትም ከክ.ል.በ በ1000 ዓ.ዓ አካባቢ ይሆናል) "ነገር ግን እግዚአብሔር ይቀበለኛልና ነፍሴን ከሲኦል እጅ ይቤዣታል።" ሲል እምነቱንና መረዳቱን የናገራል። ሲኦል በአሮጌው ኪዳን ጊዜ የነበሩ ሙታን ከአካላዊ ሞታቸው በኋላ በአጸደ ነፍስ የሚሄዱበት፣ መሲሁ እስኪመጣና ነጻ እስኪያወጣቸውም ድረስ የሚጠበቁበትና የሚከማቹበት  ቦታ ስያሜ ነው። ለምሳሌ፦ የሟቾቹን የባለጠጋውን ሰው እና የአልአዛርን ታሪክ በምሳሌ የቀረበበትን ትርክት ልብ ይሏል፣ (ሉቃስ 16፥ 19-31)። ለኃጢአተኛው የስቃዩ ስፍራ የነበረው "ሲኦል" እና ለአልአዛር የእረፍቱና የመጽናኛው ስፍራ የነበረው "የአብርሃም እቅፍ" / ገነት የአንድ ስፍራ ሁለት የተለያዩ ቦታዎች ይመስላሉ።

አብርሃምና ዘሮቹ አንድ ቀን በሚያገኛቸውና በሚለማመዱት  መንፈሳዊ ትንሳኤ፣ ይኸውም፦ ከእግዚአብሔር ጋር መታረቅ/ ወደ እግዚአብሔር ኃልዎት መመለስ ያምኑና ተስፋ ያደርጉ ነበር፣
"አብርሃም የተባለው ርስት አድርጎ ሊቀበለው ወዳለው ስፍራ ለመውጣት በእምነት ታዘዘ፥ ወዴትም እንደሚሄድ ሳያውቅ ወጣ። ለእንግዶች እንደሚሆን በተስፋ ቃል በተሰጠው አገር በድንኳን ኖሮ፥ ያን የተስፋ ቃል አብረውት ከሚወርሱ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር፥ እንደ መጻተኛ በእምነት ተቀመጠ፤ መሠረት ያላትን፥ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠብቅ ነበርና።..... አሁን ግን የሚበልጠውን እርሱም ሰማያዊ አገር ይናፍቃሉ። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካቸው ተብሎ ሊጠራ በእነርሱ አያፍርም፥ ከተማን አዘጋጅቶላቸዋልና።..... ሴቶች ሙታናቸውን በትንሣኤ ተቀበሉ፤ ሌሎችም መዳንን ሳይቀበሉ የሚበልጠውን ትንሣኤ እንዲያገኙ እስከ ሞት ድረስ ተደበደቡ፤" (እብራውያን 11፥8- 10፣ 16 እና 35)።

3ኛ/ የሐዋርያት ሥራ 2፥ 27 "  ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥" ሲል በንጉስ ዳዊት አፍ እንደተናገረ አድርጎ  ጴጥሮስ ኢየሱስን ጠቅሶ ይናገራል
"ሲኦል" የሚለው የእብራይስጥ አቻ ቃል እዚህ ላይ የግሪኩ "ሃደስ" ነው፣ ይኸውም ኢየሱስ በዳግመኛ ምጽአቱ በ70 አ.ም ላይ እስረኞችን ነጻ ለማውጣት ተመልሶ ሲመጣ ያኔ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ያጠፋው ቦታ ነው፣ "ባሕርም በእርሱ ውስጥ ያሉትን ሙታን ሰጠ፥ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ዘንድ ያሉትን ሙታን ሰጡ፥ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ተከፈለ። ሞትና ሲኦልም በእሳት ባሕር ውስጥ ተጣሉ። ይህም የእሳት ባሕር ሁለተኛው ሞት ነው።" (ራእይ 20፥ 13-14)።
የሐዋርያት የሥራ 2፥ 27 ቢያንስ ከ70 አ.ም በፊት የነበሩ ነፍሳት በስጋ  ከሞቱ ወይም አካላዊ መሞትን ከሞቱ በኋላ ወደ ሲኦል/ ሃደስ ይሄዱ እንደነበር ያረጋግጥልናል።

ከ70 አ.ም በፊት የተወለዱ ሁሉ፣ ልክ እንደ እኛ- የድህረ 70 አመተ ምህረት ላይ እንዳለን እንደ ዛሬዎቹ ሰዎች፣ ሊያደርጉት የተገባቸው ከሁለት አንድ ምርጫ ነበራቸው፦ እግዚአብሔር የተናገረውን ማመን ወይም አለማመን፤ ከዚያም በስጋ በሚሞቱበት ጊዜ፣ በ70 አ.ም የሚሆነውን የመጨረሻውን ፍርድና ውሳኔ ወደሚጠባበቁበት ሰፍራ ይሄዳሉ። በተያያዘም......
በክፍል አንድ የመግባቢያ ጥናታችን ማጠቃለያ ላይ ሕያዋን የሆኑ፣ ከእርሱ ጋር እርቅ ያደረጉ አንዳች የተለየ ነገር ቢያስቡ የሚያስገርም ይሆናል እንጂ ምንም ማድረግ አይቻልም። ስለዚህም በእርገቱና በመመለሱ መካከል በክርስቶስ ለሆነ ሕይወት በመንፈሳዊ ሁኔታ መነሳት  እውን የሚሆነውና እንዲህ ያለውን ሕይወት የሚለማመዱት በእምነታቸው ምክንያት ነው (የኤፌሶን 2፥ 1-9)። አሁንስ ታዲያ ከሃደስ መወገድ በኋላ እንዴት ነው? መንፈሳዊ ትንሳኤ አሁንም እንኳ ሕያዋን ሳለን ከእምነታችን የተነሳ ተዘጋጅቶልናል፤ በሥጋ ከሞትን በኋላ ግን መጻኢ እድላችን እውን ሆኖ እስኪታወቅ ድረስ ለመቆየት እንድ የሆነ ቦታ መሄድ አያስፈልገንም።
4ኛ/ እንደገና እብራውያን 11 39-40 ያለውን እናንብብ፣ " እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።"

እዚህ ላይ የሚወራላቸው "እነዚህም" የተባሉ ሰዎች ወይም 'እነርሱ' የሚለው ቃል የሚያመለክተው በዳግመኛ ምጽአቱ "ፍጹማን" ለመሆን "የተሰጠውን የተስፋ ቃል" ይኸውም "እግዚአብሔር ስለ እኛ (እኛ የተባሉት ጳውሎስና የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የእብራውያን ክርስቲያኖች ናቸው) አስቀድሞ ያየልንን አንዳች የሚበልጥ ነገር" ሳያገኙ ከ70 አ.ም በፊት የሞቱትን ሰዎች ነው።

"ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ"  በሚለው ንግግር ውስጥ እነዚህም" የተባሉትን ሰዎች ለብቻቸው ፍጹማን ከመሆን የሚከለክል ነገር አለው፤ ይህም እነዚያ ታማኝ የነበሩ የአሮጌው ኪዳን ቅዱሳን ሙታን እና ከ70 አ.ም በፊት በትንሳኤ ተስፋ ያንቀላፉ ክርስቲያን አማንይን፣ በ70 አመተ ምህረት ላይ በዳግመኛ ምጽአቱ መንፈሳዊ ትንሳኤን ለመቀበል ተዘጋጅተው በህይወት ኖረው  ይጠባበቁ ከነበሩቱ ቅዱሳን ተነጥለው ምነፈሳዊ ትንሳኤን የማይለማመዱ መሆናቸውን የሚያመለክት አሳብ ነው (ፊልጵስዩስ 3፥ 8- 12 ያለውን ተመልከቱ፤ ኋላ ላይ በጥልቀት እናጠናዋለን)

"ፍጹም"  በሚል ቃል የተገለጠው ኑሮ፣ ሊመጣ ባለው በመንግስቱ ውስጥ በልጁ ሕይወት አማካኝነት ሊገለጥ  ያለውን "የሚበልጥ ነገር" እንደሚያመለክት አስታውሱ (1ቆሮንቶስ 13፥ 8ጀምሮ)።

5ኛ/ 1ተሰሎንቄ 4፥ 13-17 ያለው ክፍል ከእብራውያን 11 ጋር ፍጹም በሚባል ደርጃ ሊስተያይ የሚችል ክፍል ነው፤ እስቲ አብረን እናምብበው፦ " ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፥ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።  ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና። በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና፤ እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤  ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።"
 
ጳውሎስ "እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር"  በሚልበት ጊዜ በንግግሩ የሚያመለክተው ሲጽፍላቸው የነበሩትን የተሰሎንቄን ቅዱሳንና ራሱን ጭምር ነው፣ እነርሱም ጌታ በሚመለስበት ጊዜ ሳይሞቱ በሕይወተ ስጋ ቆይተው ይኖራሉ ብሎ የሚያምናቸውን (ወይም በቀላሉ ይሆናል ብሎ የሚያስባቸውን) ነው። ጳውሎስ አንቀላፍተው ስላሉቱ በሚናገርበት ጊዜ የሚያመለክተው በስጋ ስለሞቱት፣ ነገር ግን ደግሞ ለህይወት ትንሳኤ ይነሱ ዘንድ በ70 አመተ ምህረት ላይ የሚሆነውን የመታደስን/ የመመለስን ጊዜ ሲጠባበቁ የነበሩትን በድሮ ጊዜ ስለነበሩ ቅዱሳን ነው።
ስለሆነም....  ወዳለፈው ጊዜ ስንመልከት እነዚያ ከ70 አ.ም በፊት በስጋ የሞቱ ቅዱሳን የራሳቸውን እርቅና እድሳት በተቀበሉበት በዚያው ጊዜ እነዚያም በሕይወተ ሰጋ የነበሩ ቅዱሳን የራሳቸውን ተቀብለዋል ማለት ነው።
♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦